=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ኢማድ አድዲን ኢስማኤል ኢብን ኡመር ኢብን ከሲር አል-በስሪ አዲመሽቂ የተወለዱት በ700 ዐ.ሂ ሲሆን አባታቸው የሞቱት የሰባት አመት ልጅ እያሉ ነው።
በታላቅ መንድማቸው በመታጀብ ወደ ደማስቆ አቀኑ፤ ብዙ እውቀት ከኢብን ሻኪር አል-አመዲ እና ከለሌሎችም ሻቱ።
ከሚታወቁባቸው ስራዎች መካከል አል-ቢዳያ ወኒሃያ(የመጀመሪያው እና የመጨረሻው) ይገኝበታል። የሰኺህ አል-ቡኻሪ ከፊሉን ፓርት ተንትነዋል።
በቁርአን እና በታሪክ ትንተናቸው በደንብ ይታወቃሉ። ኢብን ሐቢብ በቁርአን ትንተና የተሰማሩ ሰዎች ሁሉ መሪ ሲሉ ገልፀዋቸዋል።
ፈትዋቸው በተለያዩ አገራት ዝናን እና ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን በሰዎች ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል።
ሰኺህ ሐዲሶችን የመሸምደድ ፣ የአንድን ሐዲስ ደረጃ ፣ የታሪኮችን ታማኝነት የመገምገም እና ሰኺህ የሆኑ ሐዲስሶችን ዶኢፍ ከሆኑ ሐዲሶች የመለየት ብቃት ነበራቸው።
ኢብን ከሲር የአይን ብርሃናቸውን ያጡት ከመሞታቸው ከጥቂት ጊዜ በፊት ሲሆን የሞቱትም በ774 ዐ.ሂ ነበር። የተቀበሩትም ከጏዳቸው ከኢብን ተይሚያ ጋር ከሱፊዮች መቃብር ነበር።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|